ቻይና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡትን የምርጫ ጣልቃገብነት ክስ ውድቅ ማድረጓን ገልፃ ክሶቹንም መሰረተ ቢስ ናቸው ብላለች፡፡
ቤጂንግ ዋሽንግተን በዚህ አመት ከሚካሄደው የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ በፊት በቻይና ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ለማካሄድ እየሞከረች ነው ስትል ከሳለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን እንደተናገሩት፥ የትራምፕ ክሶች ‹‹ምንም ዓይነት›› እውነተኛ መረጃ የሌላቸው እና ቻይናን ለማጠልሸት የታለሙ ናቸው።
በሌላ በኩል ትራምፕ ቻይና ከ2020 የምርጫ ዑደት ጀምሮ የ2መቶ20 ሚሊዮን አሜሪካውያን መራጮችን ፋይል ማግኘቷን ገልጸው ድርጊቱን “በታሪክ ውስጥ ትልቁ የምርጫ መረጃ ጥሰት” በማለት ገልጸውታል።
ቃል አቀባዩ አሜሪካን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ ስለላ በማካሄድ እና በውጭ ሀገራት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ከሰዋል።
ትራምፕ በበኩላቸዉ የሲአይኤን ሪፖርት በመጥቀስ የቻይና አመራር በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ወቅት ከ2020 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት የእርሳቸውን የድል እድል ለማዳከም መፈለጉን ጠቁመዋል።
ይህ የእርስ በርስ ውንጀላ የመጣው አሜሪካውያን ለአጋማሽ ዘመን ምርጫ ወደ ምርጫ ጣቢያ ከማምራታቸው ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ ሲሆን፤ በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ያለው ውጥረት በንግድ፣ በቴክኖሎጂ እና በብሔራዊ ደህንነት ዙሪያ አሁንም እንደበረታ ነው።
ሀና ሰይፉ
ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም
