በጦርነትና ግጭት ለተጎዱ ወገኖች የሚሰጠው የጤና አገልግሎት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ እና አገልግሎት ማግኘት ላልቻሉ ማህበረሰቦች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን MSI ኢትዮጵያ አስታወቀ።

የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ አበበ ሽብሩ፥ በተለይም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የሚገኙ ተፈናቃዮች የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ቅድሚያ ተሰጥቷል ብለዋል።

ዶክተር አበበ እንደገለጹት፥በእነዚህ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታና የነዳጅ እጥረት ስራውን አስቸጋሪ ቢያደርገውም፣ ድርጅቱ በየአካባቢው ያሉ የጤና ባለሙያዎችን በማሰልጠንና ግብዓቶችን በማቅረብ አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ እያደረገ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል።

በተለይም በትግራይ ክልል የነዳጅ እጥረት ተግዳሮት በሆነባቸው ቦታዎች፣ በዚያው የሚገኙ ባለሙያዎችን በማብቃት ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉ የማድረግ ስልት እየተከተለ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ተግባር በጦርነት ምክንያት የፈረሱ የጤና መሰረተ-ልማቶችን ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *