የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለተገደሉት የአሜሪካ ወታደሮች በቀል እንደሚወስዱ ከተናገሩ በኋላ የተካሔደው ይህ ጥቃት ለ10 ተከታታይ ምሽቶች ቀጥሏል፡፡
ትራምፕ ቀደም ሲል ባደረጉት ንግግር በቅርቡ ለተገደሉት ሦስት የአሜሪካ ወታደሮች ክብር ሲባል ሰኞ ምሽት በኢራን ላይ ‹‹በጣም ከባድ››ጥቃት መፈጸሙን ገልጸው ነበር።
ለዚህ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ በሚገኙ ሁለት የነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንዲሁም በባህሬን እና ኩዌት በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ሀብቶች ላይ ጥቃት ማድረሷን የሀገሪቱ የመንግስት ዜና ኤጀንሲ ኢርና ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን በበኩላቸው ኢራን አሁን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሙሉ በሙሉ ጦርነት›› ውስጥ መሆኗን ተናግረዋል።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በባህሬን የሚገኘውን የአሜሪካው አማዞን ኩባንያ መሰረተ ልማት ኢላማ ማድረጉን አስታውቋል።
በተጨማሪም አብዮታዊ ዘቡ በባህሬን የሚገኘውን የአሜሪካው አማዞን ኩባንያ የማዕከላዊ ዳታ መሰረተ ልማት በበርካታ ክሩዝ ሚሳዔሎች በመምታት አውድሞታል ሲል የዜና ኤጀንሲው ዘግቧል።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በኤክስ ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ የቅርብ ጊዜዎቹ ጥቃቶች የኢራንን ወታደራዊ የቁጥጥር ማዕከላት፣ የባህር ላይ አቅሞችን፣ የሜሳይል እና ድሮን ማስወንጨፊያ ቦታዎችን እንዲሁም የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ኢላማ ያደረጉ መሆናቸውን ገልጿል።
ኢራን በበኩሏ ጠቃሚ በሆነው የውሃ መንገድ ለማለፍ ሲሞክሩ ጥቃት ያደረሰችባቸውን የሁለቱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ሰራተኞች ለማዳን ቡድኖች እየጣሩ ይገኛሉ ብላለች።
ሀና ሰይፉ
ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም
