ሎስ ፓላሲዮስ ኢ ቪያፍራንካ በስፔን ከሲቪያ በስተደቡብ አቅጣጫ የምትገኝ አነስተኛ ከተማ ናት፤ 400 ሺህ ህዝብ ብቻ ይኖርባታል፡፡
ስፔን የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ስታነሳ ታዲያ የቡድኑ አባላት ከነበሩት መካከል ፋቢያን ሩይዝ እና ጋቪ ከዚህች አነስተኛ ከተማ ነው የተገኙት፡፡
ሁለቱ ተጨዋቾች ትናንትና ወደ ትውልድ ከተማቸው ሎስ ፓላሲዮስ ኢ ቪያፍራንካ ሲመለሱ ታዲያ በነዋሪዎቿ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ከዚህም በላይ ግን ነገሩን አስገራሚ ያደረገው ጉዳይ ላስመዘገቡት ድል የተበረከተላቸው ሽልማት ነው፡፡
የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ሃላፊ ከተማቸው በቲማቲም ምርቷ የምትታወቅ መሆኗንና በተለያዩ አጋጣሚዎች ታሪክ ለሚሰሩ ጀግኖቻቸው ይህንን ምርት በሽልማት መልክ እንደሚየጣበረክቱ ጠቅሰው ለሁለቱ ተጨዋቾችም ይሄንኑ ሽልማት አበርክተውላቸዋል፡፡
ሽልማቱ የተበረከተላቸው በኪሏቸው መሰረት ነው፡፡ በዚህም መሰረት የፓሪስ ሴንት ዠርሜኑ ሩይዝ 85 ኪሎግራም እንዲሁም የባርሴሎናው ጋቪ 68.5 ኪሎ ግራም የቲማቲም ምርት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የቀድሞው የስፔን ብሔራዊ ቡድን መስመር ተጫዋች ሄሱስ ናቫስ እ.ኤ.አ በ2010 የዓለም ዋንጫን በማንሳት ከሎስ ፓላሲዮስ ኢ ቪያፍራንካ ከተማ የተገኘ የመጀመሪያው ተጫዋች በነበረበት ወቅት ተመሳሳይ ሽልማት ተበርክቶለት ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም ናቫስ እና የአሁኑ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ሩይዝ ከስፔን ጋር የ2024 አውሮፓ ዋንጫን ካሸነፉ በኋላም ተመሳሳይ የቲማቲም ስጦታ ተበርክቶላቸው ነበር።
የከተማዋ የስፖርት ማዕከል በናቫስ ስም የተሰየመ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ለተቀዳጁት ስኬት እውቅና ለመስጠት የእግር ኳስ ሜዳዎች በሩይዝ እና በጋቪ ስም እንዲሰየሙ ከውሳኔ ላይ መደረሱን የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት አስታውቋል።
ምስጋናው ታደሰ
ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም
