ዘመን ባንክ አጠቃላይ የሀብቱ መጠን 1መቶ16 ቢሊየን ብር መድረሱን ገለጸ

ባንኩ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡንም አስታዉቋል

የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ ቢምር ባደረጉት ንግግር፤ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የላቀ ውጤት መገኘቱን ገልጸው፤ ለዚህ ስኬት ለባንኩ የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ከ14 ቢሊየን ብር በላይ፤ አጠቃላይ ገቢው 17.8 ቢሊየን ብር፣ ጠቅላላ ካፒታሉ 26 ቢሊየን ብር መድረሱን ተነግሯል፡፡

የባንኩ የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ32 በመቶ አድጎ 85.4 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን፤ የውጭ ምንዛሬ ግኝቱ ደግሞ 6መቶ98 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሆኗል፡፡

ዘመን ባንክ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 1መቶ42 ማሳደጉን አስታዉቋል፡፡

ባንኩ ባለፉት 18 ዓመታት የሥራ አድማሱን በማስፋትና በአንድ ቅርንጫፍ ከሚሰጥ ኮርፖሬት አገልግሎት በመነሳት ቅርንጫፎቹን በማብዛት ለሁሉም ደንበኞቹ ይበልጥ ተደራሽ ሆኗል፡፡

ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *