ሐማስ የትጥቅ መፍታት ስምምነቱን መቀበሉን አስታወቀ

ሐማስ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያስታወቁትን «የሰላም ቦርድ» እቅድ በመቀበል በጋዛ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን አስታውቋል።
 
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ቦርዱ በጋዛ ከሚንቀሳቀሱት ሐማስ እና ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ጋር «ሙሉ በሙሉ ትጥቅ የመፍታት» ስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አድርገዋል።
 
አንድ ከፍተኛ የሐማስ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ቡድኑ በጋዛ ትጥቅ ለመፍታት የቀረበውን እቅድ የተቀበለ ሲሆን፣ ዝርዝሩን የያዘ ኦፊሴላዊ መግለጫ በቅርቡ እንደሚወጣ አስታውቀዋል። በጉዳዩ ላይ እስካሁን ከእስራኤል በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም።
 
ፕሬዚዳንት ትራምፕ አክለው እንዳሉት፣ «ትጥቅ የመፍታቱ ሂደት ሲጠናቀቅ» የእስራኤል ጦር ከጋዛ ይወጣል፤ ይህ ስምምነትም «ጋዛ በመጨረሻ በአዲሱ የፍልስጤም አስተዳደር ለመመራት የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን ወሳኝ እርምጃ ነው» ብለዋል።
 
በአሜሪካ አነሳሽነት በተዘጋጀው የጋዛ የተኩስ ማቆም እቅድ ሁለተኛ ምዕራፍ ውስጥ የሐማስ ትጥቅ መፍታት እና የጋዛ ድጋሚ ግንባታ ጉዳዮች የተካተቱ ናቸው።
 
በሌላ በኩል ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ«ትሩዝ ሶሻል» ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፡ «ይህ ስምምነት የትራምፕን ባለ 20 ነጥብ እቅድ ለመተግበር የተደረገ ትልቅ ታሪካዊ እርምጃ ነው። ስምምነቱ በጥንቃቄ በተዋቀሩ ምዕራፎች የሚከናወን ይሆናል። ትጥቅ የመፍታቱ ሂደት እንደተጠናቀቀ፣ የእስራኤል ጦር ይወጣል ፤ ዓለም አቀፉ የሰላም ማስከበር ኃይልም ከአዲሱ የፍልስጤም ፖሊስ ጋር በመተባበር የጋዛንና የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ይረከባል» ብለዋል።
 
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በንግግራቸው አሸማጋይ ለነበሩት ግብፅ፣ ቃጣር እና ቱርክ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
 
የግብፅ መንግሥት መገናኛ ብዙኃንን ጠቅሶ ኤኤፍፒ እንደዘገበው ፣ በሁለተኛው ምዕራፍ የተኩስ ማቆም እቅድ ላይ የሚያተኩረው የአሸማጋዮች ስብሰባ በካይሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
 
ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *