ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብና የተጎሳቀለችውን ምድር ለማንሰራራት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ መካሄድ ጀምሯል።

“ኑ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ታሪካዊ ዘመቻ፤ በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተይዟል።
 
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በሰጡት መግለጫ፤ እስከ ማለዳው 3፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ 200 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን አስታውቀዋል።
 
በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው በመሳተፋቸው 68 ሺህ ሄክታር መሬት በችግኝ መሸፈን ተችሏል።
 
ሚኒስትሯ በዚሁ መግለጫቸው፦ “ኢትዮጵያውያን ዝቅ ብለው ለምድር አደራ ይሰጣሉ፤ ምድርም የተሰጣትን አደራ እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች”  ሲሉ የሕዝቡን ታላቅ ንቅናቄና የተፈጥሮ ፍቅር አድንቀዋል።
 
ይህ ታላቅ ሀገራዊ የችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ዛሬ እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ድረስ በመላው ሀገሪቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
 
ሐምሌ 27 /2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *