የማይንማር የዲሞክራሲ መሪ እና የናቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ኦንግ ሳን ሱ ቺ ከሁለት ዓመት ተኩል እስር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውጭ አካል ጋር ተገናኙ።

የአገሪቱ ወታደራዊ መንግሥት ባወጣቸው ፎቶዎች ላይ፣ ዕድሜያቸው 81 የሆኑት ኦንግ ሳን ሱ ቺ ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ልዑክ ጋር ተገናኝተው በጥሩ ጤንነት እና ዘና ብለው ታይተዋል።
 
መሪዋ እ.ኤ.አ. በ2021 በመፈንቅለ መንግሥት መሪዎች ከተያዙ በኋላ በእስር ላይ የቆዩ ሲሆን፣ በቅርቡ ግን የእስራት ጊዜያቸው ተቀንሶ ወደ መኖሪያ ቤት እስር መዛወራቸው ይታወቃል።
 
ልጃቸው ኪም አሪስ እና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እሳቸው በሕይወት ስለመኖራቸው ማረጋገጫ እንዲሰጥ ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡
 
መሪዋ ከቀይ መስቀል ልዑክ ጋር ስለተወያዩበት ዝርዝር ጉዳይ የተገለጸ ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
 
ሐምሌ 27 /2108 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *