ይህንን የአቅርቦት ችግር ለመፍታት ወደ ውጭ የሚላከውን የኤክስፖርት መጠን ከመቀነስ ይልቅ ምርትና ምርታማነትን በስፋት ማሳደግ እንደ ዋነኛ መፍትሄ የተቀመጠ ሆኗል።
ይህንን ያሉት የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።
በዚህም መሰረት ለቡና ልማት አመቺ ሆነው ሳለ እስካሁን ያልለሙ ሰፊ የሀገሪቱን መሬቶች ወደ ማምረት ማሸጋገር ከተቻለ፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ማሟላት ብቻ ሳይሆን የገበያ ዋጋውን በዘላቂነት ማረጋጋት እንደሚቻል አቶ ግዛት ጠቁመዋል።
አቶ ግዛት ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ሌላው ያነሱት ጉዳይ የአየር ንብረት ለውጥ ለኢትዮጵያ የቡና ምርት አዲስ ዕድል ይዞ የሚመጣ መሆኑን ነው።
ይህ ለውጥ የኢትዮጵያ የቡና ምርት ላይ በበጎ መልኩ ሊንጸባረቅ እንደሚችል ተናግረዋል።
በ2050 ከዓለማችን አምስት ቀዳሚ የአረቢካ ቡና አምራች ሀገራት (ብራዚል፣ ኮሎምቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሆንዱራስ እና ፔሩ) መካከል ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጡ የተሻለ ተጠቃሚ ትሆናለች ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ለቡና ልማት ተስማሚ የሆነው የመሬት ስፋት 4 በመቶ ብቻ መሆኑንና በ2050 ግን ይህ መጠን በሦስት እጥፍ አድጎ 12 በመቶ እንደሚደርስ ተናግረዋል።
ሳራ ዮሐንስ
ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም
