የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአርሶ አደር ይዞታዎች ላይ ጥሎት የነበረውን የካርታ ማስተላለፍ እገዳ አነሳ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአርሶ አደር ይዞታዎች ላይ ሲሰጥ የነበረውን የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገልግሎት ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታወቀ።

ቢሮው ቀደም ሲል እገዳውን የጣለው አርሶ አደሩን ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶች ለመጠበቅ እንዲሁም የይዞታ ዋስትናውን ለማረጋገጥ በወጣ መመሪያ መሰረት እንደነበር አስታውሷል።

ሆኖም እገዳው ጸንቶ በቆየባቸው ጊዜያት በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ክፍተቶች መታየታቸውንና ከባለይዞታዎች ዘንድ በርካታ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ሲቀርቡ መቆየታቸውን ገልጿል።

እነዚህን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት እና ለቀረቡት አቤቱታዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ሲባል፣ ከነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እገዳው በይፋ መነሳቱ ተገልጧል።

ለዓለም አሰፋ

ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *