በደቡባዊ ሶሪያ፣ አብዛኛው ነዋሪ የድሩዝ ማህበረሰብ በሆነባት ሱዌዳ ግዛት፣ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው ታጣቂ ቡድኖች መካከል ግጭት መከሰቱ ተነግሯል ።
የሶሪያ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ፣ በዚህ ግጭት 10 የመንግስት የጸጥታ አባላት ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።
ግጭቱ የተቀሰቀሰው በጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው ባሉ ታጣቂዎች መካከል በነበረ የቃላት ምልልስ እና አለመግባባት እንደሆነ ተገልጿል።
የሱዌዳ ግዛት ለዓመታት ከመንግስት ጋር በተያያዘ በተቃውሞዎች እና አልፎ አልፎ በሚከሰቱ ግጭቶች የምትታወቅ ሲሆን፣ የዛሬው ግጭትም በቀጠናው ያለውን ውጥረት ዳግም እንዳባባሰው ተዘግቧል።
ስለ ታጣቂዎቹ ጉዳት እስካሁን የተገለጸ መረጃ የለም።
ልዑል ወልዴ
ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
