የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የግንባታ ዘርፉን አሰራር ዘመናዊ ለማድረግ ከግል ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ገለጸ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ዶ/ር) አዲስ የተዘጋጀውን የግንባታ ፊዚካል አፈጻጸም መለኪያ ስታንዳርድ ባስተዋወቁበት መድረክ ላይ ሲናገሩ፤ “ተቋሙ በደንብ ቁጥር 524/2014 የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት በመደመር መርህ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል” ብለዋል።
አዲሱ የሪፖርት ማዕቀፍ ስታንዳርድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የቁጥጥርና የተጠያቂነት ባህል እንዲሰፍን እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ለዘርፉ ተዋንያን የሚሰጠው ስልጠናም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይ በየተቋማቱ ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
አዲስዓለም አበበ
ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም
