ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መንገድ በተያዘው የዌስት ባንክ ግዛት ውስጥ ከሚገኙ የእስራኤል ሰፈራዎች በሚመጡ ምርቶች እና አገልግሎቶች ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል ተገልጿል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤድ ሚሊባንድ ውሳኔውን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትያቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ሚኒስትሩ በቅርቡ በዩኬ እና በእስራኤል መካከል ያለው ግንኙነት ‹‹እንደገና እንደሚቃኝ›› መናገራቸው ይታወሳል።
እነዚህ ሰፈራዎች በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ሕገ-ወጥ እንደሆኑ ቢታሰብም፤የዩኬ ማዕቀብ እርምጃ የመጣው እስራኤል በተያዘው ግዛት ውስጥ ለ1ሺ2መቶ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ጨረታ ባወጣችበት ወቅት ነው።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዩኬ ላይ ሊወሰድ ስለሚችል የአጸፋ እርምጃ ቢጠየቁም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
በሌላ በኩል አሜሪካ የዩኬን ማዕቀብ የመጣል ውሳኔ የምትቃወም ሲሆን፤በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የተለያዩ የአሜሪካ ክፍለ ሀገራት በዩኬ ላይ የአጸፋ እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ።
ሀና ሰይፉ
ጳጉሜ 03/2018 ዓ.ም
