በኢንዶኖዥያ 243 ሰዎችን የጫነች መርከብ በመስጠሟ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

“ቪርጎ ትራንስፖርት 8” የተሰኘችው ይህች መርከብ ከምሥራቅ ጃቫ ወደ ደቡብ ካሊማንታን በመጓዝ ላይ እያለች ነው በመጥፎ የአየር ሁኔታ ምክንያት በጃቫ ባሕር ውስጥ የሰጠመችው።

በመርከቧ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች መካከል 213ቱ መንገደኞች ሲሆኑ 30 ደግሞ የመርከቧ ሰራተኞች ናቸው ተብሏል ።

እስካሁን በተደረገ የነፍስ አድን ጥረት 107 ሰዎችን በሕይወት ማዳን ተችሏል።

የጠፉትን 130 ሰዎች ለመፈለግም 280 ባለሙያዎች በስፍራው ተሰማርተው የፍለጋ ሥራቸውን ቀጥለዋል።

ልዑል ወልዴ

መስከረም 5/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *