46 የመንግሥት ዩንቨርስቲዎች ለዳግም ምዝገባ ሪፖርታቸዉ በማስገባት፤  ክፍቶቻቸዉን እንዲሞሉ ግብረ መልስ እንደተላከላቸዉ ተነገረ

የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ ሂደትን በመንግሥት ዩንቨርሲቲዎች መጀመሩን ተናግሯል።

ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተዉ ባለስልጣኑ  በግል ተቋማት ላይ ሂደቱን አስጀምሮ የቆየ ቢሆንም፣ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የዳግም ምዝገባ ሂደት መጀመሩን ነግረዉናል።

ዶ/ር አህመድ በሀገሪቱ ካሉት የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች 46ቱ ራሳቸዉን ገምግመዉ ሰነድ አዘጋጅተው መላካቸዉን ገልፀዋል።

ዩንቨርስቲዎቹ ያቀረቡት ሰነድ በባለሙያዎች መገምገሙን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ የታዩባቸዉ ክፍተቶችን እንዲያርሙ ግብረ መልስ መላኩን ተናግረዋል።

በሂደቱ ያጓደሏቸዉን መስፈርቶች በ45 ቀናት ዉስጥ አሟልተዉ እንዲያቀርቡ እና ማሟላት ያልቻሉበትን ሁኔታ እንዲያብራሩ ይደረጋል ተብሏል።

ባለስልጣኑ ዩንቨርስቲዎቹ ባቀረቡት ሪፖርት እና  በማስተካከያ ግብረ መልሱ በኋላ  ያሟሏቸዉን መስፈርቶች ለመገምገም የመስክ ምልከታን እንደሚያደርግ ዶ/ር አህመድ አስረድተዋል።

የዳግም ምዝገባ ሂደቱ ዩንቨርስቲዎቹ በትምህርት ጥራት ዙሪያ ያለባቸዉን ክፍተቶች ለመለየት እና ክፍተቶቹ እንዲያስተካክሉ ያግዛል ተብሎለታል።

ቁምነገር አየለ

መስከረም 6/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *