አባይ’ን ጨምሮ በአፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ታላላቅ ወንዞች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ያደረጉ የፓናል ዉይይቶች የሚደረጉበት ነዉ በተባለዉ ኮንፈረንስ ከ20 በላይ ሀገራት እንደሚሳተፉ ተገልፆል።
በአየር ንብረት ለዉጥ እና ከአህጉሪቱ የህዝብ ቁጥር መጨመር አንፃር በዉሃ አጠቃቀም እና አስተዳደር ዙሪያ የመፍትሄ አቅጣጫን የሚጠቁሙ የጥናት ወረቀቶች የሚቀርቡበት ይሆናል ተብሏል ፡፡
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አፍሪካ የዉሃ ማኔጅመንት የልህቀት ማእከል ከዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመሆን አዘጋጅቶታል በተባለዉ ኮንፈረንስ ከመጪዉ መስከረም 11- 13 ለሶስት ቀናት እንደሚካሄድ አዘጋጅ ኮሚቴዉ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግሯል።
የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስር ያለዉ የአፍሪካ የዉሃ ማኔጅመንት የልህቀት ማእከል ዳይሬክተር ኘሮፌሰር ፈለቀ ዘገየ በአፍሪካ አንድ ሰዉ በቀን ማግኘት አለበት የሚባለዉን የዉሃ መጠን እያገኘ አለመሆኑን በመግለፅ የዉሃ አጠቃቀም ፍትዊነት ላይ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንዲቻል ኮንፈረንሱ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
60 በመቶ ያህል ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ የዉሃ አካላት አስተዳደር ምን መምሰል እንዳለበት በተለያዩ ምሁራን ገለፃ እንደሚቀርብ ኘሮፌሰር ዘለቀ ገልፀዋል።
የዉሃ አካላት ስነምህዳር ፥ የመጠጥ ዉሃ እና በዉሃ ራስን መቻል በሚሉ እና ሌሎች ነጥቦች ዉይይት የሚደረግባቸዉ አጀንዳዎች መሆናቸዉ ተነግሯል።
ከ 3 መቶ በላይ የተለያዩ ሀገራት ተሳታፊዎች ይኖሩታል የተባለዉ ኮንፈረንስ በመጪዉ ሰኞ በአድዋ ሙዚየም የሚካሄድ ይሆናል።
ቁምነገር አየለ
መስረም 8/2019 ዓ.ም
