ተቋሙ በላከው መረጃ መሠረት፤ አገልግሎቱ የተሰጠው በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 5 ዞኖች (ምስራቅ ጉጂ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና) ሲሆን፤ አባወራዎችን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል አግኝተዋል።
በዚህም የአካባቢው ነዋሪዎች ይደርስባቸው ከነበረው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንግልት ተላቀው ጥራት ያለው አገልግሎት ማግኘት ችለዋል።
ተቋሙ ከዋናው ግሪድ ርቀው ለሚገኙ አካባቢዎች የሶላር ሚኒ-ግሪድ ፕሮጀክቶችን የዘረጋ ሲሆን፤ እ.ኤ.አ በ2030 የሀገሪቱን 100% ሕዝብ (65% ከዋናው ግሪድ እና 35% በአማራጭ ኃይል) የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጻል።
መስከረም 8/2019 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ላለፉት 10 ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይል ሳያገኙ የቆዩ ከ5 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን የኃይሉ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
