የሁቲዎች የተቀናጀ ግስጋሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ ዋሽንግተን ለሪያድ ድጋፍ ስትነሳ ለንደን ደግሞ “አለሁ” ብላለች

በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማፂያን የቀይ ባህር ዳርቻዎችን እና ስልታዊ ስፍራዎችን ለመቆጣጠር የሚያደርጉትን ወታደራዊ ግስጋሴ አፋጥነዋል። ቡድኑ ሳዑዲ አረቢያን “ዋና ጠላቴ ናት” ሲል በይፋ ካወጀ እና በባህር ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ ከጣለ ማግስት ጀምሮ፣ በሳዑዲ ከተሞችና የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚያደርሰውን የድሮንና የሜሳይል ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል።
 
አማፂያኑ በሳዑዲ ርዕሰ ከተማ ሪያድ ላይ የሜሳይል ጥቃት መፈጸማቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ የሪያድ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጡት ምላሽ የለም።
 
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከዋሽንግተን በኩል ያልተጠበቀ ውሳኔ ተሰምቷል፦ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሁቲዎች ላይ ሊሰነዘር ተዘጋጅቶ የነበረውን የአሜሪካ የአየር ጥቃት በመጨረሻዋ ደቂቃ እንዲሰረዝ አድርገዋል። በዚህም አሜሪካ ከሳዑዲ አረቢያ እና ከየመኑ ፕሬዝዳንት ራሺድ አል-አሊሚ የቀረበላትን ቀጥተኛ የወታደራዊ እገዛ ጥያቄ ሳይትቀበለው ቀርታለች።
 
የሁቲዎች ድርጊት የመካከለኛው ምስራቅን ቀውስ የበለጠ በማባባስ የዓለምን የኃይል አቅርቦት አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ሮይተርስ ዘግቧል።
 
በሌላ በኩል፣ የታላቋ ብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ ቡርንሀም ሀገራቸው ለሳዑዲ አረቢያ አስቸኳይ ወታደራዊ ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል።
 
በመከላከያ ሚኒስትራቸው ዌስ ስተርሊንግ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ኤድ ሚሊባንድ ምክረ-ሀሳብ ላይ ተመስርተው ውሳኔውን ማሳለፋቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በቆጵሮስ ከሚገኘው የሮያል ኤር ፎርስ (RAF) ጦር ሰፈር የሚነሱ የብሪታንያ አውሮፕላኖች ለሳዑዲ የጦር ጄቶች በበረራ ላይ ሳሉ ነዳጅ የመሙላት አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
 
ይህ ለሳምንታት ይዘልቃል የተባለው ድጋፍ በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚጀምር ተነግሯል።
 
መስከረም 12/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *