የ2019 የኢሬቻበዓል «ኢሬቻለሀገራዊመግባባት» በሚልመሪቃልበታላቅስኬትይከበራል

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጃሚላ ሲምቢሩ፥ የ2019 የኢሬቻ በዓል በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር ገልፀዋል::

የኦሮሞ አባ ገዳ ህብረት በበኩሉ የዘንድሮው  የኢሬቻ በዓል «ኢሬቻለሀገራዊመግባባት» በሚል መሪ ቃል እንዲከበር መወሰኑን ያሳወቀ ሲሆን በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አረጋግጧል።

በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ወይዘሮ ጃሚላ ሲምቢሩ ፤ የዘንድሮው በዓል ከምንጊዜውም በላይ ልዩ የሚያደርገው ሀገራዊ አንድነትንና ግንባታን መሠረት ያደረገ በመሆኑ ነው ብለዋል።

ሀገሪቱን በውይይትና በመግባባት ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ሀገራዊ የምክክር መድረክ በተካሄደበት ወቅት መከበሩም ለበዓሉ ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል ብለዋል።

አክለውም፣ መንግስት የህዝብ አደራውን አጠናቆ ሀገራዊ ምርጫ የተካሄደበት እንዲሁም የተመረጠው አዲስ መንግስት በሚመሰረትበት ዋዜማ ላይ የሚከበር በመሆኑ በዓሉን ታሪካዊ እንደሚያደርገው አብራርተዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞን ኢኮኖሚ የመገንባትና የባህል ህዳሴን የማረጋገጥ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊዋ፤ ለዚህም ሲባል የኢሬቻ በዓል የሚከበርባቸው መልካዎች(የውሀ ቦታዎች)ለዓለም አቀፍ ደረጃ አርአያ በሚሆን መልኩ እንዲለሙና እንዲገነቡ ትልልቅ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።

በመጨረሻም የ2019 የኢሬቻ በዓል በሙሉ ሰላምና በፍቅር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሀና ሰይፉ

መስከረም 12/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *