ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ በስድስት ወራት ውስጥ ከ15.5 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ ተባለ

4.9 ቢሊዮን ብሩ ለአስቸኳይ እህል ግዢ እንደተመደበም ተገልጿል

በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ15.5 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በኮሚሽኑ የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ማስተባበሪያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሻግሬ ተሾመ እንደገለጹት፤ ፈንዱ የተሰበሰበው መላው ሕዝብ በተሳተፈበት አሰራር ሲሆን፣ ዜጎች በባንክ የገንዘብ ዝውውር ከሚያደርጓቸው ጥቃቅን የሳንቲም መዋጮዎች ጭምር የተገኘ ነው።

አቶ አሻግሬ አክለውም ከተሰበሰበው 15.5 ቢሊዮን ብር ውስጥ የፈንዱ ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ 4.9 ቢሊዮን ብሩ ለአደጋ ጊዜ የምግብ እህል ግዢ እንዲውል መመደቡን አስታውቀዋል።

ይህ አሰራር አገሪቱ ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት ተላቃ በራስ አቅም ፈጣን የአደጋ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችላትን አቅም የፈጠረ መሆኑንም ገልጸዋል።

አዲስዓለም አበበ

መስከረም 18/2019 ዓ.ም.

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *