ድርጅቱ በጦርነቱ ምክንያት የአካል ጉዳተኞች ቁጥር እየጨመረ ስለሚሄድ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታዉቋል፡፡
በኢትዮጵያ በአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት ምክትል ስራ አስኪያጅ ቲም ስቲን ሀገራቸዉ ለኢትዮጵያ የምታደርገዉን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
የድርጅቱ የወጣቶች ፕሮግራም አስተባባሪ ያደሳ አስፋዉ በበኩላቸዉ፣ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸዉን ዜጎች ለመድረስ እንደሚሰሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ፕራይድ በተሰኘዉ ፕሮጀክቱ ድጋፍ ሲያደርግላቸዉ የነበሩትን 750 የአካል ጉዳተኞች በቴክኒክና ሙያ የትምህርት መስክ በቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
የፕራይድ ፕሮጀክት አስተባባሪ ወይዘሮ ቤተልሄም ዝናዬ በአካል ጉዳተኞች ላይ ያተኮሩ ከ21 በላይ ፕሮጀክቶችን ቀርጸዉ እንደሚሰሩ ነግረዉናል፡፡
የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸዉ በተለይም በትግራይ፤ በአፋርና በአማራ ክልሎች በስፋት እንደሚሰራ ገልጿል።
በአባቱ መረቀ
ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም
