በኢትዮጵያ ከ7 ሺህ በላይ ህፃናትና ታዳጊዎች ቀዶ ጥገና እየተጠባበቁ ይገኛሉ ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ ከ7 ሺህ በላይ ቀዶ ጥገና የሚጠባበቁ ህፃናትና ታዳጊዎች መኖራቸውን የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል አስታውቋል።

ከልብ ህመም እና ከደም ስር መጥበብ እንዲሁም ከአፈጣጠር ጋር በተያያዘ በሚከሰት የጤና እክል ምክንያት፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመምጣት የቀዶ ጥገና ወረፋ እንደሚይዙ የማዕከሉ ዳይሬክተር ሚክሎን መንግስቱ ተናግረዋል።

በዓለማችን ብሎም በሀገራችን በተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያትም ከዚህ ቀደም ወደ ኢትዮጵያ ይላኩ የነበሩ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን አሁን ላይ በቀላሉ ማግኘት አልተቻለም ተብሏል፡፡

በማዕከሉ በህክምና ቁሳቁስ እጥረት እና በተለያዩ እክሎች ምክንያት ቀዶ ጥገናውን ለማድረግ የሚጠባበቁ ህፃናት ከወረፋው አስቀድሞ ህይወታቸው እያለፈ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ላለፉት 30 አመታት፤ ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የልብ ህሙማን ታካሚዎችን በመላክ የልብ ቀዶ ህክምና እና የደም ስር መጥበብ ህክምናን ሲያደርግ ቆይቷል።

ማዕከሉ 3 ሺህ ለሚሆኑ ታካሚዎች ያለምንም ክፍያ የህክምና አገልግሎት ከተለያዩ ልበ ቀና ከሆኑ ግለሰቦች እና ሀገር በቀል እንዳሁም ከሀገር ወጭ በሚደረግ እርዳታ ማከናወን ችሏል ነው የተባለው።

ህብረተሰቡ ማዕከሉን ለማገዝ በ6710 ላይ ok ብሎ በመላክ በአንድ ብር አንድ ልብ ያድን ዘንድ በማእከሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *