በግጭት የተጎዱ የስርዓተ-ፆታ ጥቃት ተጎጂ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት በዛሬው እለት ተፈርሟል።

ለሁለት ዓመት እንደሚተገበር የሚጠበቀዉ ይህ ፕርጀክት የኢትዮጵያ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ከዩኒሴፍ እና ከጄፔጉ ጋር ነዉ።

ከተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የህፃናት መረጃ ድርጅት እና ጃፓይጎ ጋር ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የደሰረባቸዉን ሴቶች እና ህፃናት ምላሽ መስጠት የሚያስችል የደሰሳ ጥናት፣የስርዓተ ፆታ ጥቃት መከላከል እንዲሁም የፆታዊ ጥቃት ምላሽ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት የሁለት ዓመት የኮንትራት ዉል ተፈራረመዋል።

በአገራችን በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ ለማልማትና በአካባቢዎቹ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ፣ በዓለም ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል በተደረሰ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት የሚተገበተር ፕሮጀክት ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በትግራ፣በአማራ፣በኦሮሚያ፣በአፋር እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ባሉ 40 ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ በስድስት ዋና ዋና አገልግሎቶች ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን፣ ጥቃት ለደረሰባቸዉ ሴቶች እና ህፃናት አገልግሎትን ማሻሻል፣የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ማስፋት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ስራዎችን እንደሚሰራ ሚኒስትሯ አስታዉቀዋል።

ይህ ፕሮጀክት በተለይም በግጭቱ ምክንያት ለፆታዊ ጥቃት የተጋለጡ ሴቶችና ህፃናትን መደገፍ ላይ ትኩረት አድርጓል ነው የተባለው።

የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር በፆታዊ ጥቃት ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ በጋራ ለመስራትም ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *