በፈረንሳይ በማዕከላዊ ፓሪስ ከባድ የተባለ የነዳጅ ፍንዳታ ተከስቶ 37 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸዉ እና ወደ 2 መቶ 70 የሚጠጉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታዉ ተገኝተዉ እሳቱን ለማጥፋት ሲጥሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በአደጋዉ አራት ሰዎች ከባድ የሚባል ሁኔታ ዉስጥ መግባታቸዉ የተገለጸ ሲሆን 2 ሰዎች ደግሞ ጠፍተዉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፍለጋ እያካሄዱ መሆኑን የፈረንሳይ መንግስት አስታዉቋል፡፡
የፈረንሳይ የአገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ‹‹ ከአደጋዉ በፊት ምንም ዓይነት የማስጠንቀቂያ ደዉል ባለመሰማቱ አደጋዉ እንዴት እንደተፈጠረ እስካሁን ምንም ያወቅነዉ ጉዳይ የለም፣ ነገር ግን እያጣራን እንገኛለን›› ብለዋል፡፡
በአደጋዉ ስፍራ ከተገኙ ተጎጂዎች በሚደረግ የመረጃ ማሰባሰብ አደጋዉ እንዴት እንደተፈጠረ ለማወቅ እንሞክራለን ሲሉም አክለዋል፡፡
የፓሪስ ከተማ አስተዳደር ከአደጋዉ ለተረፉ ሰዎች ዕርዳታ የሚያደርግ ምላሽ ሰጪ ቡድን አቋቁሞ የአደጋ ጊዜ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የሲ ኤን ኤን ዘገባ ያሳያል፡፡
በእስከዳር ግርማ
ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም
