በኢትዮጵያ ከ4 መቶ ሺህ በላይ የኩላሊት ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው የኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
የኩላሊት እጥበት ከሚያስፈልጋቸው ከ4 መቶ ሺህ በላይ የኩላሊት ታማሚዎች ውስጥ ህምክናውን የሚያገኙት ከ 5 ሺ ያልበለጡ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡
ህክምናውን እንዲጠባበቁ ከሚያደርጋቸው ምክንያች ውስጥ ደግሞ አገልግሎቱን የሚሰጡ ተቋማት ቁጥር አነስተኛ መሆን አንዱ ምክንያት ተደርጎ ተጠቅሷል፡፡
በኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት አገልግሎትን የሚሰጡ የግል እና የመንግስት የህክምና ተቋማት 48 ናቸው፡፡
የኩላሊት የጤና እክል እያደረሰ ያለውን የጤና ጉዳት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት ፣ የኩላሊት እጥበት ዋጋን ተመጣጣኝ እና ከክፍያ ነፃ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ሰለሞን አሰፋ ለኢትዮ ኤፍኤም ገልጸዋል፡፡
ማህበሩ በመንግስት ድጋፍ በተደረገለት 1 ሺህ 410 ካሬ ሜትር ላይ ግዙፍ ህንፃ የማስገንባት ስራ ለማሰራት እቅድ ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ ሰለሞን፣ ይህንን ለማሳካት ህብረተሰቡ ወደ 8582 ላይ ok ብሎ በመላክ ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።
በእሌኒ ግዛቸው
ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም
