ከሰሞኑ መጠነኛ መረጋጋት አሳይቶ የነበረው የአትክልት ዋጋ በዚህ ሳምንት ከፈተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ታዝቧል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም በጎጃም በረንዳ አካባቢ በሚገኘው አራት መንታ የአትክልት ገበያ ዛሬ ጠዋት ላይ ባደረገው ቅኝት አንድ ኪሎ ቀይ ሽንኩርት እስከ 80 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል።
ቲማቲም ከሽንኩርትም በላይ እስከ 90 ብር ሲሸጥ ተመልክተናል፡፡ ቃሪያም ከቲማትም ጋር በተመሳሳይ ዋጋ እየተሸጠ ነው፡፡

በተደረገው ቅኝት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል የተባለው ድንች በኪሎ እስከ 30 ብር ይሸጣል፡፡
ባሳለፈነው ሳምንት እስከ 250 ይሸጥ የነበረው ነጭ ሽንኩርት የ50 ብር ጭማሬ አሳይቶ ዛሬ እስከ 300 ብር እና ከዛ በላይ ሲሸጥ ተመልክተናል፡፡
ይህ ዋጋ በጎጃም በረንዳ አካባቢ በሚገኘው አራት መንታ የአትክልት ገበያ ዛሬ ጠዋት ላይ ያለውን ግብይት ብቻ የሚመለከት ነው፡፡
እርስዎም የታዘቡትን ሊያካፍሉን ይችላሉ፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም
