በሚንስቴሩ ከተፈጠሩ የስራ እድሎች 74 በመቶ የሚሆነው በኢንተርፕራይዞች ነው——የስራ ክህሎት ሚኒስትር ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ያሉ ሲሆን 74 በመቶ የሚሆነው የስራ እድል መፍጠራቸውንም የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናግረዋል።

በዛሬው እለት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ብቁ- አብቁ ሲል ከሚዲያ ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የበቃ ዜጋ ለመፍጠር ያሉትን  ችግሮች በመለየት መፍትሄዎቻቸዉ ላይ በጋራ ለመስራት ያስችላል የተባለለት የጋራ ምክክር መድረክ ነው የተካሄደው።

በመድረኩም ላይ በተቋሙ ስለተፈጠሩ የስራ እድሎች የተነሳ ሲሆን ከተፈጠሩ የስራ እድሎች መካከል  74 በመቶ የሚሆነው የስራ እድል  በኢንተርፕራይዞች መፈጠሩ ነው የተገለጸው።

ቀደም ሲል  መንግስት 10 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ  በጅቶ ለስራ ፈጠራ አስተዋፅኦ የተደረገ ቢሆንም የተፈለገዉ ለዉጥ አለመገኘቱ ተገልጿል። ።

ለዚህም ማልማት፣ማብቃት፣ማስተዳደር ላይ ለሚሰራዉ ስራ ጠንካራ የሆነ አጋዥ አካላት ያስፈልጋል ሲሉ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናግረዋል።

በመድረኩ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት፣ከኢንዱስትሪዎች ጋር፣ከቴክኒክና ሙያ እንዲሁም ከዉጭ ሀገር የስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ ፅሁፍ ቀርበው ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *