በስልጤ ዞን በቅበት ከተማ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም እየተሰራ ይገኛል ተባለ፡፡

ከአንድ ወር በፊት በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በርካታ ሰዎች መፈናቀላቸውን እና ለችግር መጋለጣቸው መገለጹ ይታወሳል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ ስራዎችን የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከተማ አስተዳደሩን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ጉባኤው ከሁሉም ቤተ እምነቶች የተውጣጡ የሃማኖት አባቶችን፣ ወደ ስፍራው አቅንተው የማጣራት ስራዎችን እንዳከናወኑ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

የማጣራት ስራውን ተከትሎ የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እና የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ የሚቻልባቸው ስራዎች መሰራታቸውን፣ በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ በነበረው ግጭት ሳቢያ ለጉዳት የተዳረጉ እና የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ እና፣ የህግ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ሲሉ የጉባኤው ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገልፀዋል።

ከእዚህ በተጨማሪ የተዋቀረው ኮሚቴ ተፈጥረው የነበሩ ችግሮችን በመለየት፣ ከአካባቢው የህብረተሰብ ክፍል ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር ምክክር ማድረጉን ዋና ፀሃፊው ገልፀዋል።

በቀጣይም መሰል ችግሮች እንዳይፈጠሩ ለማድረግ ሁሉም ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *