ወላጆችን በተለያዩ ምክንያት ማጣት ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎች መሠል ችግሮች ሲያጋጥሙ ሰዎች ለሱሰኝነት ለድብርት እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይዳረጋሉ ይህም ደግሞ ለጸጸት እንደሚዳርጋቸውም ይገለጻል፡፡
አቶ ብሩክ ዩሃንስ የስነ ልቦና ባለሞያ ናቸው፡፡
እርሳቸው እንደሚሉት፣የምንተገብራቸው ጉዳዮችን ጥቅም እና ጉዳት ላይ ጊዜ ወስዶ አገናዝቦ አለመወሰን፣ ምክንያታዊ ሆኖ አለመሆሰን፣ በሰዎች ላይ ጸጸትን ሊያስከትል እንደሚችል ያነሳሉ፡፡
የደስታ፣ የብስጭት እንዲሁም የሀዘን ስሜት በሰዎች ላይ የሚስተዋል ቢሆንም
-ስሜታዊ ሆኖ ማሰብ ፣
-የጓደኛ አቻ ግፊት
-አልኮል መጠጣት
-የአደንዛዥ እጽ መጠቀም ለጸጸ ት እንደ መነሻ ምክንያት ሊጠቀሱ ይችላሉ ብለዋል፡፡
ለምን አደረኩ ብሎ እራስን መውቀስ ጠቃሚ ቢሆንም ትናንት ላይ ከመኖር ይልቅ ስለ ነገ መልካም ነገሮች ማሰብ ይጠቅማል የሚሉት ባለሞያው፣ ለዚህም ከትናንት መጥፎ የህይወት ገጠመኞች ትምህርትን በመውሰድ ለነገ አዲስ ህይወት መዘጋጀት በሰዎች ዘንድ ሊለመድ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡
አንዳንዶች ትናንት በገጠማቸው የህይወት መጥፎም ሆነ ጥሩ ገጠመኞች ተምረው እንደሚያልፉ የሚገልጹት ባለሙያው ነገር ግን አሁንም ድረስ ባለፈ የህወወት ታሪካቸው ተሸፍነው የሚኖሩ እንዳሉ አብራርተዋል፡፡
የሚጸጸቱ ሰዎች ላይ
-የመበሳጨት፣
-ያለመረጋጋት
-የመጨነቅ ምልክቶች እንደሚስተዋሉ ገልጸው፣ ከሚጸጽታቸው ጉዳይ ወይም በተደጋጋሚ አእምሯቸው ላይ እየተመላለሰ የሚረብሻቸውን ጉዳይ ጊዜ በመውሰድ ሊረዱት አልያም በጉዳዩ ላይ የባለሞያን ምክር ማግኘት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።
ከመጥፎ ስሜቶችን ለመውጣት እንደየሰው ጥንካሬ ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በቅድሚያ ግን እራስን ከመውቀስ ይልቅ ለእራስ ይቅርታ ማድረግ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በእሌኒ ግዛቸው
ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም
