የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እስራኤልን አስጠነቀቁ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እስራኤል በጋዛ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እያደረሰች በምትገኘው የቦምብ ጥቃት ሃገሪቱን ማስጠንቀቃቸው ተሰምቷል፡፡

እስራኤል ግጭቱ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ በጦርነቱ ላይ ምንም ተሳትፎ በሌላቸው ዜጎች ላይ በምታደርገው ጥቃት አለም አቀፍ ድጋፎች እያጣች እንደምትገኝ ባይደን ተናግረዋል፡፡

በጋዛ ውስጥ እስራኤል ጥቅም ላይ እያዋለች ከምትገኛቸው መሳሪያዎች መካከል፣ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአለም አቀፍ የስምምነት መመሪያዎችን የጣሱ መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡

እስራኤል አሁንም በጋዛ የምታደርገውን ድብደባ የቀጠለች ሲሆን፤ይህ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ እስራኤል በአለም ሃገራት ዘንድ ተቀባይነትን ይበልጥ እንደምታጣ አስጠንቅቀዋል፡፡

እስራኤል ከተጠቀመችባቸው 29,000 የአየር እና የመሬት ጥቃቶች ውስጥ ከ40 እስከ 45 በመቶ ያህሉ መመሪያ የጣሱ መሆናቸውን የCNN ዘገባ አመላክቷል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ታህሳስ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *