በኢትዮጵያ “ድርቅ እንጂ ረሃብ” አልተከሰተም አለ መንግስት

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ወደ ረሃብ ተቀይሯል የሚሉ መረጃዎች ሌላ ዓላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሚያዘዋውሯቸው እንጂ ሣይንሳዊና እውነተኛ መሠረት የላቸውም ሲሉ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ገለጹ።

በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ ነው የሚል መረጃ በማሠራጨት ላይ ያሉ ወገኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ሲሉ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ለተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች መንግሥት 11 ቢሊየን ብር መድቦ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *