የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ አዛዥ ጄነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ አዲስ አበባ ገቡ።

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሰራዊት አዛዥ ጀነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሃሜቲ) በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጀነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሃሜቲ) አዲስ አበባ ሲደርሱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አቀባበል እንዳደረጉላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒቴር አስታውቋል።

ካሳለፍነው ሚያዚያ ወር ጀምሮ ከሱዳን ብሔራዊ ጦር ጋር እየተዋጉ ያሉት የፈጥኖ ደራሽ ሀይል አዛዥ ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ወይም ሄመቲ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በኡጋንዳ ቆይታ አድርገው ነበር።

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *