በኬንያ የሱዳን አምባሳደር ከማል ጁባራ በአስቸኳይ ወደ ካርቱም እንዲመለሱ የሱዳን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መጥራቱን አስታዉቋል፡፡
የሱዳን መንግስት አምባሳደሩን ከናይሮቢ የጠራዉ የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስተዳደር ለሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ሃይል ሀምዳን ዳጋሎ የሞቀ አቀባባል በማድረጉ ነዉ ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫዉ ኬንያ ያደረገችዉ ለአማጺ ሃይሉ እዉቅና እንደመስጠት ይቆጠራል ሲል ወቅሷል፡፡
የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ ከሰሞኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ማድረጋቸዉ የአልቡርሃንን ጦር አስቆጥቷል፡፡
ጦሩ የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን መሪ የሚያስተናግዱ ሀገራት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡም እያሳሰበ ነዉ፡፡
በአባቱ መረቀ
ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ.ም
