ኮርፖሬሽኑ በዚሁ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን አሰልጥኖ በትናንትናው እለት የምስክር ወረቀት የመስጠት መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ነበር።
በማዕድን ኮርፓሬሽን አዘጋጅነት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የመጀመሪያ ዙር እና ለአምስት ቀናት የቆየ ሲሆን ኢትዮጵያ ብዙ የማዕድን ሀብቶች እንዳሏት እና ያሉዋትን ሃብቶች በአግባቡ ለማልማት እና በዘርፉ ያሉትን ክፍተቶችን ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ በመርሀ ግብሩ ላይ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ እንደደረሰ እና የስራ አጦች ቁጥርን ለመቀነስ አንድ ላይ ስራዎችን እንደሚሰሩ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጧል፡፡
በስልጠናው ላይ ጥሩ እውቀት እንዳገኙ እና ኢትዮጽያ በማዕድኑ ዘርፍ ጥሩ አቅም እንዳላት ግንዛቤ እንዳገኙ ሰልጣኞቹ ተናግረዋል።
በስልጠናው ወቅት አሰልጣኞቹ በቂ እውቀት ያላቸው በመሆኑ በቂ ልምድ እንዳገኙበት እና ኢትዮጵያ ውስጥ የማዕድን እና ጌጣጌጥ ኢዱስትሪው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ መረዳታቸውንም ሰልጣኞቹ ተናግረዋል።
ኮርፓሬሽኑ በቀጣይነት ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም አምራች እና ገዥን በማገናኘት ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ተነግሯል።
በሀመረ ፍሬው
ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም
