የኬንያ መንግስት ሐገሪቱን ለሚጎበኙ ኢትዮጵያዉያን መንገደኞች አዲስ የመግቢያ ፈቃድ ማጣሪያ ደንብ (Visa Waiver) ማውጣቱ ተሰምቷል።

ሁለቱ ሐገራት ከብዙ ዓመታት በፊት ባደረጉት ስምምነት መሠረት ከአንዱ ሐገር ወደ ሌላዉ የሚጓዝ መንገደኛ የመግቢያ ፈቃድ (Visa) አያስፈልገዉም ነበር።

የኬንያ መንግስት አዲስ ባወጣዉ ደንብ መሠረት ግን ከግሪጎሪያኑ 2024 ጀምሮ ወደ ኬንያ የሚገቡ ኢትዮጵያዉያን መንገደኞች ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የተወሳሰበና ረጅም ጊዜ የሚወስድ የኦን-ላይን ፎርም መሙላት አለባቸዉ።

ኬንያ ነባሩን ሕግ የቀየረችበት ምክንያት በዝርዝር አልጠቀሰም።

ኢትዮጵያ መንግስትም ነባሩን ደንብ ስለመቀየር-አለመቀየሩ አላስታወቀም።

በእንግሊዝኛ የሚታተመዉ ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገበዉ ግን
የኢትዮጵያ መንግስት አዲሱን የኬንያን ደንብ እያጠና ነዉ።

ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *