በአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ መብራቶችን ህግ መጣስ ለ አደጋ መንስኤ ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታወቋል፡፡
በመጀመሪያው እሩብ አመት 49ሺ ዘጠና የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ቀይ የትራፊክ መብራት እንደተከሰሱም ተገልጿል ።
የ2016 ዓ.ም እሩብ አመት ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ሞት እና ከባድ አደጋ በመጠኑ መቀነስ ቢያሳይም ቀላል ጉዳት እና ንብረት ላይ የሚደርስ አደጋ መጨመሩን ሰምተናል ።
በአዲስ አበባ ፓሊስ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሙያና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ እርቀትን ጠብቆ አለማሽከርከር እና ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር የንብረት አደጋውን እንዳባባሰው ገልፀዋል።
ፍላጎትና ንብረቱ ስላላቸው ብቻ መንጃ ፍቃድ ሳይኖራቸው የሚያሽከረክሩ ግለሰቦች እንዲሁም ሀሰተኛ መንጃ ፈቃድ አሰርተው የሚያሽከረክሩ ሹፌሮች ላይ ሰፊ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝም ኢንስፔክተር ስለሞን ተናግረዋል፡፡
ሀመረ ፍሬዉ
ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም
