በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በድርቅ በተጎዱ አከባቢዎች ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ መቃወስ እንዳሳሰበው ኦቻ ገለፀ።

በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ባሉት በአፋር ፣ አማራ፣ ትግራይ እና ኦሮምያ አከባቢዎች ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ መቃወስ አሳስቦኛል ሲል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /በምህጻሩ ኦቻ/ ገልጿል።

ድርቁን ተከትሎ የሚከሰቱ ችግሮች በመበራከታቸው በእነዚህ አከባቢዎች ለሚገኙ 4 ሚሊየን ዜጎች የምናደርገውን የሰብዓዊ ድጋፍ መጨመር ይገባናል ነው ያለው ቢሮው።

በቁጥር ብዙ የሆኑ እና ተደራራቢ ችግሮች የሰዎችን ችግር የመቋቋም አቅም አዳክመዋል ብሏል።

በዚህም ሚሊየኖች ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው ዘላቂ ለሆነ ዕርዳታ ጠባቂነት ተጋልጠዋል ነው ያለው።

እኛ እና አጋሮቻችን የአገሪቱን መንግስት እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን በተወሰነ የገንዘብ ድጋፍ እየረዳን እንገኛለን ሲል ገልጿል።

ባለፈው ዓመት ከጥር -ህዳር በነበረው ጊዜ ከአጋሮቻችን ጋር በጋራ በመሆን 12 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች ዕርዳታ ማድረስ ችለናል ብሏል።

አሁን ላይም ቢሆን ችግሩ ከዚህ የከፋ ከመሆኑ በፊት ፈጣን ምላሽ ቢገኝ መፍትሄ መሆኑ ተገልጿል።

በ2023 ከተጠየቀው የ4 ቢሊየን የሰብዓዊ ድጋፍ ምላሽ ውስጥ ማግኘት የተቻለው
1.3 ቢሊየኑን ብቻ ነው።

እስከዳር ግርማ

ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *