ታቦታት ወጥተው በሚገቡበት እንንዲሁም በሚያርፉበት አካባቢ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል አለ ኮሚሽኑ፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከጥምቀት በአል አከባበር ጋር በተያያዘ ለታቦታት ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ ብሏል፡፡

ታቦታት ከደብራቸው ወጥተው ወደ ሚያርፉበት ቦታ በሚያቀኑበት አካባቢ የተበጠሰ የኤልክትሪክ ገመድ መኖሩ አለመኖሩ መረጋገጥ አለበት ሲል ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡

በተያያዘም በጥምቀተ ባህሩ ቦታ በድንኳኖች አካባቢ የሚዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች በሰዉ ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታዉ በጥንቃቄና በባለሞያ መሆን እንደሚገባዉም የተጠቆመ ሲሆን ጧፍና ሻማ በሚበራ ጊዜም ተመሳሳይ ጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት ተላልፏአል።
አንዳንድ ቦታዎች ላይ ዝቅ ያሉ የኤልክትሪክ መስመሮች በመኖራቸው አደጋ ሊከሰት ይችላል ያለው ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት በዚህ ምክንያት ያጋጠመ አደጋ ነበር ብሏል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በየሰፈሩ ያሉ አስተባባሪዎች ተቆፍረው ያለተደፈኑ ጉድጓዶች መኖራቸውም ማረጋገጥ አለባቸው ብለዋል፡፡

አቶ ንጋቱ ከከተራ እና ከጥምቀውት በአል አከባበር ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩትን አደጋዎች መቆጣጠር እንዲያስችል እነዚህን ስልክ ቁጥሮች ተጠቀሙ ብለዋል፡፡
ለእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት እነዚህን ስልክ ቁጥሮችመጠቀም ይቻላል፡፡
የማዕከል መረጃ
939 ወይም 011-1-55-53-00
011-1-56-86-01
የአራዳ ቅርንጫፍ
011-1-56-02-49
011-1-56-02-50
ቂርቆስ ቅርንጫፍ
011-4-66-34-20
011-4-66-34-21
አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ
011-2-76-91-45
011-2-76-91-46
ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ
011-4-42-55-63
011-4-42-55-64
አቃቂ ቅርንጫፍ
011-4-34-00-96
011-4-34-30-63
ቦሌ ቅርንጫፍ
011-6-63-03-73
011-6-63-03-74
ኮልፌ ቅርንጫፍ
011-3-69-60-85
011-8-69-68-69
ጉለሌ ቅርንጫፍ
011-2-73-07-31
011-2-73-06-53
ለሚኩራ ቅርንጫፍ
011-6-68-08-46
011-6-68-07-60
በአደጋ ጊዜ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ፈጥነዉ ያሳዉቁ

ሔኖክ ወ/ገበርኤል

ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *