የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ፅጌወይን ካሳ ፤ ” የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበረባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው ተነስቷል ” ብለዋል።
ማህበራቱም ግንባታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ ኃላፊዋ ገልፀዋል።
በ40/60 እና በ20/80 ተመዝጋቢ የነበሩ እና በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተዘጋጁ 57 ማህበራት በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።
