የአገው ብሄራዊ ሸንጎ የክልሉ መንግስት ለሠላም ያለው ቁርጠኝነት አነስተኛ ነው አለ

ፓርቲውን የሚወክል ከክልሉ መንግስት ጋር የተደረሰ ምንም አይነት ስምምነት አለመኖሩንም የአገው ብሄራዊ ሽንጎ ምክትል ሊቀመንበር ተናግረዋል ።

በአካባቢው የዞን ከተሞች አንፃራዊ ሰላም ያለ ቢመስልም ከከተማ እሩቅ የሆኑ ሰዎች ግን ሁለንተናዊ ችግሮች ውስጥ ናቸው ተብሏል ።

የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ፍትህ አለው አባይ ፣በጋራ እንስራ የሚሉ ጥያቄዎችን ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ እያቀረብን ቢሆንም የክልሉ መንግስት ምላሽ አልሰጠንም ሲሉ ወቅሰዋል ።

አገው ብሄራዊ ሸንጎ ከፌዴራል እንዲሁም ከክልሉ መንግስት ጋር ችግሮቹ በሰከነ መንፈስ እንዲፈቱ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ እንደሆነ እና ይሄንንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ምክትል ሊቀመንበሩ ገልፀዋል ።

የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር የተፈራረመው የሰላም ስምምነት የአገው ብሄረሰብን ፍላጎት አያሳካም ሲል የአገው ብሄራዊ ሸንጎ ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ሀመረ ፍሬው

የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *