አራት ኪሎ የሚገኘው የእግረኞች መሸጋገሪያ ድልድይ ጉዳት ደረሰበት፡፡

አራት ኪሎ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የሚገኘው የእግረኞች መሸጋገሪያ ድልድይ ጉዳት ደርሶበታል፡፡

አደጋውን ተከትሎም ከአምሥት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ እና ከአራት ኪሎ ወደ አምሥት ኪሎ ያለው መስመር ዝግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተሽከርካሪዎችም አደባባይ ሳይደርሱ ተለዋጭ መንገድ እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው፡፡

ጉዳት የደረሰበትን ድልድይ ለማንሳት ጥረት እየተደረገ ሲሆን÷ ለጊዜውም የትራፊክ እንቅስቃሴው በተለዋጭ መንገድ እየተከናወነ ነው፡፡
የጉዳቱ ምክንያት እስካሁን ባይገለጽም አሁን ላይ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል ተብሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *