በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ምስጋና ፋንታው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት፣
በመዲናዋ ትክክለኛ የመንገድ አጠቃቀም ያልተከተሉ ከ1 ሺህ 370 በላይ እግረኞች መቀጣታቸውን ገልፀውልናል
በዚህ ቅጣትም ከፍተኛውን ቁጥር የሚወስዱት ወንዶች ሲሆኑ ከ1370ዎቹ ተቀጪዎች 1328 ወንዶች ሲሆኑ 42ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን አቶ ምስጋናው ፋንታሁን ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በዚህም 1370 እግረኞች የገንዘብና የማህበራዊ አገልግሎት ቅጣት ተላልፎባቸዋል ሲሉ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡
ከእግረኞች ቅጣትም ወደ 38 ሺ መሰብሰቡን ያነሱት አቶ ምስጋናው፤
የገንዘቡ ትንሽነት እንዳለ ቢሆንም ብዙዎቹ ግን የማህበራዊ ሃላፊነት ቅጣት እንደተጣለባቸው ገልፀውልናል።
የቁጥጥር ሥራው አሁንም እንደሚቀጥል የገለጹልን አቶ ምስጋናው እግረኞች የወጣውን የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395 ማክበር ካልቻሉ ቁጥሩ ከዚም ከፍ ሊል እንደሚችል ነግረውናል።
በለዓለም አሰፋ
ሐምሌ 04 ቀን 2016 ዓ.ም
