በ2016 በጀት አመት 1 መቶ 17 ሺህ 860 ከፍልሰት ተመላሽ ዜጎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉን የሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በዘንድሮ ዓመት ከተለያዩ ሀገሮች፤ ከሱዳን 47 ሺህ 746 ፣ ከየመን 2 ሺህ 482 ፣ ከኦማን 2 ሺህ 326 ፣ እንዲሁም ከሳውዲ አረቢያ 65 ሺህ 306 ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የተናገሩት፤ በሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላል እና የተመላሽ ዜጎች ደንብ ድጋፍ እና ክትትል መሪ ስራ አስፈጻሚ ደረጄ ተግይበሉ ናቸው፡፡
ከሚያዚያ ወር ጀምሮ 70 ሺህ ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ በእቅድ ተይዞ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ፤ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ በሁለት ዝግጅቶች 65 ሺህ 306 ከፍልሰት ተመላሽ ዜጎችን ወደ ሀገር ውስጥ አንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከፍልሰት ለሚመለሱ ዜጎች የመለየት እና ድጋፍ ማድረግ፣ ከቤተሰብ ለተነጠሉ ህጻናት ቤተሰብ የማፈላለግ እና ከፍልሰት የተመለሱትን ወደ አከባቢያቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
በ2015 በጀት ዓመት 1መቶ 1 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ ፤ 1 መቶ 30 ሺህ ዜጎችን ወደ ሀገር ውስጥ መመለሳቸውን ያስታወሱ ሲሆን፤ በሚያዚያ ወር የተጀመረው 70 ሺህ ዜጎችን ከፍልሰት የመመለሱ ስራ አሁንም እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡
በእሌኒ ግዛቸው
ሐምሌ 04 ቀን 2016 ዓ.ም
