የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የተከሰቱ ወረርሽኞችን እየተቆጣተርኩኝ ነው አለ ::

በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ኮሌራ፣ ኩፍኝ፣አባ ሰንጋ ፣ ወባ እንዲሁም የእከክ  ወረርሽኞች  በዚህ አመት ከፍተኛ  ጉዳት ሊያደርሱ ሞክረዋል ተብሏል።

  የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊው አቶ አሰፋ ነጋሽ ኮሌራ ጥቅምት ወር ላይ የተከሰተ ሲሆን ወደ 274 የሚደርሱ ሰዎችን ሲያጠቃ የ4 ሰዎች ህይወት  ማለፉን አንስተው የኩፍኝ ወረርሽኝ ደግሞ 1800 የሚደርሱ ሰዎችን እንዳጠቃ እና በዚህም ከ15 በላይ ህጻናት ህይወታቸው እንዳለፈ ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም በኮሌራ እና በኩፍኝ የህፃናት ህይወትን ያጣነው  እኛ የማንደርስባቸው የፀጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ናቸው ብለዋል፡፡

በተከሰተው የአባ ሰንጋ ወረርሽኝም ከ5ሺህ በላይ እንስሳት እንደሞቱ  እና በሽታው ከእንስሳት ወደ ሰው እየተላለፈ ከ300 ባላይ ሰዎችን ማጥቃቱን ነግረውናል።

እንዲሁም ከ4 ሺህ  በላይ  የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በእከክ እንደተጠቁ  እና በተከሰተው የወባ ወረርሽኝ ደግሞ 36 ሺህ  የሚሆኑ ሰዎች መጠቃታቸው አንስተዋል፡፡

ወረርሽኞቹ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ የመቆጣጠር ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙም አቶ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *