የህዝብ ክምችት በሚበዛባቸው አምስት ቦታዎች ላይ 250 አውቶቢሶች ተመደቡ።

በአዲስ አበባ ከተማ በስራ መግቢያና መውጫ ሰአቶች ህዝብ ይበዛባቸዋል ተብለው በተለዩ አምስት ቦታዎች ተጨማሪ አውቶቢሶች መመደባቸው የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር እጸገነት መክብብ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የሰልፍ ቆይታ ጊዜ ለመቀነስ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና ከከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ጋር በመሆን ተጨማሪ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል ብለዋል።

ወደ አገልግሎት የገቡት ተሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት የሚታየውን የህዝብ ትራንስፖርት የሰልፍ ቆይታን ጊዜ ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብሏል።

በከተማው የህዝብ ክምችት ይበዛባቸዋል ተብለው በተለዩ አምስት ቦታዎች ማለትም መገናኛ፣ ቦሌ፣ አራትኪሎ፣ ፒያሳና ሜክሲኮን በልዩ ሁኔታ 250 አውቶቢሶች መመደባቸው ታውቋል።

በከተማው የትራንስፖርት አማራጭ ማሳደግ በመቻሉ እስከ ምሽት 2:00 ሰአት ይቆይ የነበረውን የቆይታ ጊዜ እስከ 11:40 ሙሉ በሙሉ ሰልፉን ማጠናቀቅ መቻሉን ገልፀዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *