በኢትዮጵያ በአቬሽን ዘርፍ እየሰሩ ያሉ የህግ ባለሙያዎች ከሁለት አይበልጡም ተባለ።

በኢትዮጵያ የስራ ፍቃድ ወስደው የህግ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ከ5ሺህ በላይ የህግ ባለሙያዎች ቢኖሩም በአቬሽን ዘርፍ የህግ አገልግሎት እየሰጡ አይደለም ተብሏል።

የስራ ፍቃድ ከወሰዱት 5ሺህ የህግ ባለሙያዎች ውስጥ የአቬሽን ዘርፉን በጥልቀት ተገንዝበው የህግ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት ከሁለት እንደማይበልጡ ነው የተገለጸው።

ኢትዮጵያ ከምትኮራባቸው ዘርፎች መካከል የአቬሽን ኢንዱስትሪ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች የህግ ባለሙያዎች በዚህ ዘርፍ አይተሳተፉ አይደለም ነው የተባለው።

ባለሙያዎቹ በዘርፉ የማይሳተፉበት ዋነኛ ምክንያት በዘርፍ የዳበረ እውቀት ስለሌላቸው እና የመስራት ፍላጎት ቢኖራቸው እንኳን እድሉ ባለማግኘታቸው የተነሳ ነው ተብሏል።

የኢትዮ አሊያንስ አድቮኬትስ የህግ ጥብቅና እና የማማከር ድርጅት ጠበቃ እና የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ ከተማ አዳነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የአቬሽን ዘርፉ የሚመራው በአለም አቀፍ ህጎች እና ስምምነቶች መሆኑን ተናግረው እነዚህ ህጎችን ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል ብለዋል።

አቬሽን ዘርፉን የሚመራው ተቋምም እራሱን በማጠሩ ምክንያት የህግ ባለሙያዎች እነዚህ ህጎችና ስምምነቶች እንዳያውቁ ከማድረጉ በተጨማሪ በዘርፉ እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል ብለዋል።

በጥብቅና እንደዚሁም በማማከር ስራ ላይ የሚገኝው ኢትዮ አሊያስ አድቮኬትስ ድርጅት የህግ ባለሙያዎች በአቬሽን ዘርፍ ያለባቸውን የእውቀት ክፍተት ለመቅረፍ በዘርፉ እውቀት ባለቸው ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ አቶ ከተማ ለጣበያችን ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 8 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *