የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆባይደን በትራምፕ ላይ የተሞከረዉን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የፖለቲካዉ ውጥት እንዲቀንስ ጥሪ አቀረቡ ፡፡

ፖለቲካ በፍፁም የዉጊያ ሜዳ መሆን የለበትም ፈጣሪ የግድያ አዉድማን አጥብቆ ይከላከላል ሲሉ ነዉ ጆባይደን ጥሪ ያቀረቡት ፡፡

በቅዳሜው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸው በኃላ አሜሪካውያን “በአንድነት እንዲቆሙ” ጠይቀዋል።

ባይደን ሀገሪቱ ወዴት እያመራች እንደሆነ እና ማን ይመራታል በሚለው ላይ አለመግባባት ቢኖርም ፖለቲካ “የሰላማዊ የውይይት መድረክ” መሆን እንዳለበት ደጋግመው አሳስበዋል።

የእኛ እምነት የቱንም ያህል ጠንካራ ቢሆን ወደ ሁከት መግባት የለብንም ሲሉ አክለዋል፡፡

ለጥቃቱ ሪፐብሊካኖች ጣታቸዉን በዲሞክራቲኮች ላይ እየቀሰሩ ይገኛል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ሐምሌ 8 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *