የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በ2016 በጀት አመት በተለያዩ ጥፋቶች ላይ ገብተው ትግኝተዋል ባላቸው 50 ሺ 6 መቶ 5 የሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስጃለው አለ፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ነጋዴዎች ያለንግድ ፍቃድ ሲነግዱ የተገኙ 13 ሺ 3 መቶ 56 ነጋዴዎች ፣ባልታደሰ ፈቃድ ሲነግዱ የተገኙ 6 ሺ 2 መቶ 13 ፣የንግድ ፍቃዳቸውን ሳይሰቅሉ የተገኙ 5 ሺ 8 መቶ 80 የሚደርሱ ነጋዴዎች ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም ያለደረሰኝ ሲነግዱ የተገኙ 3ሺ 2 ነጋዴዎች፣ የዋጋ ዝርዝር ባለመለጠፍ 10 ሺ 3 መቶ58 ፤ከአድራሻ ውጪ የሚነግዱ 2 ሺ 8 መቶ 98፣ ከዘርፋቸው ውጪ ሲነግዱ የተገኙ 2 ሺ 5 መቶ11፣ምርት አከማችተው የተገኙ 63 ነጋዴዎች እና የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈባቸው ምርት በመሸጥ ላይ የነበሩ 84 የሚደርሱ ነጋዴዎች እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል መሆናቸውን ነግረውናል፡፡

በ2016 በጀት አመት 4መቶ 29 ሺ 1 መቶ 51 በሚሆኑ የንግድ ድርጅቶች ላይ የበር ለበር ክትትል መደረጉን አንስተዋል ፡፡

ከተወሰዱት እርምጃዎች ውስጥ 29 ሺ 2 መቶ 52 የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ 21 ሺ 1 መቶ 76 የታሸጉ የንግድ ድርጅቶች ሲሆኑ ምርት እንዳያመርቱ የታገዱ 22 እና ምርታቸው እንዲወገድ የተደረጉ 82 የንግድ ድርጅቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ገብተው ከነበሩት 50 ሺ 6 መቶ 5 ነጋዴዎች መካከል ወደ ህጋዊነት እንዲመለሱ የተለያዩ እርምጃ ከተወሰደ በኋላ 45 ሺ 7 መቶ 89 የሚሆኑት አሁን ላይ ስራችውን መስራት የጀመሩበት ሁኔታ ምኖሩንም አንስተዋል፡፡

ህገውጥ ንግድ ዋጋ እንደሚስከፍል ያነሱት አቶ ሰውነት ህጋዊ ሆኖ መስራት የሚቻልበት ምቹ ሁኔታዎች እያሉ ህገወጥ ሆኖ መስራት እራስንም ቤተሰብንም ለጉዳት ይዳርጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ሐምሌ 09 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *