ሾተላይ በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት በአለመጣጣም ምክንያት የሚከሰት ነው ።
ይህ ሾተላይ የተባለቀዉ ችግር በሃገራችን ኢትዮጵያ በሁሉሙ አከባቢ የሚከሰት ስሆን በገጠራማዉ የሃገራችን ክፍል ያሉ እናቶች ደሞ ለዚህ ችግር ተጋላጭ ይሆናሉም ተብሏል ፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ በቅዱስ ጳዉሎስ ሆሰፒታል የማህፀን እና የፅንስ እስፔሻሊሲት የሆኑትን ዶክተር ፍላጎትን ታደሰን ጠይቀናል ።
ዶከተር ፍላጎትም ሾተላይ በተፈጥሮ የሚከሰት እንጂ በጤና ችግር የሚከሰት አደለም ብለውናል።
ሾተላይ ለምን ይከሰታል?
የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
- “A”
- “B”
- “AB”
- “O” ተብለው ይጠራሉ።
- በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው ተብሏል ።
ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል።
አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ ነው።
ይህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።
እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።
ከነዚህ መካከል
-በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር
-በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ
-የፅንሱ የደም ማነስ
-ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
- ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ
-በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ
ሾተላይ እንዴት ይታከማል?
*Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት:-
- ባለቤቷ Rh positive ከሆነ
- ውርጃ ካጋጠማት
-ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት - ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ ካጋጠማት
- በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
-በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ
Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።
-በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር ወይንም 28 ሳምንት ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።
-Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል።
-ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል።
በመጨረሻም ሾተላይ የሚስት ደም Rh negative ከሆነ እና የፅንሱ ደም Rh positive ከሆነ እና የባል ደም ደግሞ Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም ተብሏል ።
ዶ/ር ፍላግት ታደሰ እንዳሉት እናቶች በዕርግዝና ወቅት ቀድመው መመርመር እና የደም አይነታቸውን ማወቅ እንዲሁም ክትትል ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
በልዑል ወልዴ
ሐምሌ 09 ቀን 2016 ዓ.ም
