በቻይና የገበያ ማዕከል በተከሰተ የእሳት አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ፡፡

የሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳስታወቀው፤ በቻይና በተከሰተው የእሳት አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ብዙዎች ተጎድተዋል።

የእሳት አደጋው የተከሰተው በቻይና በምዕራባዊ በሲቺዋን ግዛት በዚጎንግ ከተማ በሚገኝ የገበያ ማዕከል ላይ ነው።

የደረሰውን አደጋ ለመቆጣጠር 300 የሚሆኑ የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ወደ ስፍራው ማምራታቸው ተጠቁሟል።

ከዚህ ቀደም በደቡብ ምስራቅ የቻይና ግዛት በሚገኝ ህንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ39 ዜጎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ነው።

በእሌኒ ግዛቸው

ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *